Ecclesiastes 9

የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ

1ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም። 2ጻድቃንና ኀጥኣን፣ ደጎችና ክፉዎች
ሰብዓ ሊቃናት (አቍዊላ) ቨልጌትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ፣ ዕብራይስጡ ግን ክፉዎች የሚለው የለም
፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የማያቀርቡ፣ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው።

ለደጉ ሰው እንደ ሆነው ሁሉ፣
ለኀጢአተኛውም እንዲሁ ነው፤
ለሚምሉት እንደ ሆነው ሁሉ፣
መሐላን ለሚፈሩትም እንዲሁ ነው።
3ከፀሓይ በታች በሁሉም ላይ የሚሆነው ክፋት ይህ ነው፤ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። በዚህም ላይ የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወት እያሉም በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ በመጨረሻም ወደ ሙታን ይወርዳሉ። 4በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው
ወይም ታዲያ የሚመረጠው ምንድን ነው? ለሕያዋን ሁሉ ተስፋ አለ
፤ በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና!

5ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤
ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤
መታሰቢያቸው ይረሳል፤
ምንም ዋጋ የላቸውም።
6ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣
ቅናታቸውም ከጠፋ ቈይቷል፤
ከፀሓይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣
ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም።
7ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር እግዚአብሔር ደስ ብሎታልና። 8ዘወትር ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘወትር በዘይት ቅባ። 9እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጕም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና። 10እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኀይልህ ሥራው፤ ልትሄድበት ባለው መቃብር
በዕብራይስጥ ሲኦል ማለት ነው
ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።

11ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤

ሩጫ ለፈጣኖች፣
ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤
እንጀራ ለጥበበኞች፣
ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣
ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤
ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።
12ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤

ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣
ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣
ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣
በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

ጥበብ ከሞኝነት ይበልጣል

13እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፤ 14ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት። 15በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም። 16ስለዚህ፣ “ጥበብ ከኀይል ይበልጣል” አልሁ፤ ሆኖም የድኻው ጥበብ ተንቋል፤ ቃሉም አልተሰማም።

17ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣
ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።
18ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤
ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።
Copyright information for AmhNASV